yekibirtesfatheologicalcollege
| Forum role | Member since | Last activity | Topics created | Replies created |
|---|---|---|---|---|
| Member | Aug 20, 2023 (2 years) |
2 years | 1 | 0 |
- Forum role
- Member
- Member since
Aug 20, 2023 (2 years)
- Last activity
- 2 years
- Topics created
- 1
- Replies created
- 0
Bio
ክርስቶስ የክብር ተስፋ የካህናት ማሰልጠኛ ማዕከል
Christ the Hope of glory prisitehood training institute
ራዕይ
ክርስቶስን የሚመስሉ አገልጋይ መሪዎችን በቤተክርስቲያን ማየት
ተልዕኮ
ተልዕኳችን ለማኅበረሰቡ ፋይዳ ያላቸው አገልጋይ መሪዎችን በማዘጋጀት ቤተ ክርስቲያን የተሰጣትን የእግዚአብሔር መንግሥት ተልዕኮ ለማስፈጸም አጋር የልዕቀት ተቋም ኾኖ መገኘት ነው።
ዓላማዎች
🛐ቃለ እግዚአብሔር በሙላት የሚገኝባቸው፥ ለማስተማር፥ ለመስበክና ለማስተዳደር ብቁ የኾኑ አገልጋይ መሪዎችን በአለም ዙሪያ ለምትገኘው የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ማፍራት፤
🛐በቅዱሳት መጻሕፍት ዕውቀት የበሰሉ፥ በክርስቲያናዊ ነገረ መለኮት አስተንትኖት የዳበረ መረዳት ያላቸው እና የእግዚአብሔርን ቃል ጤናማ በኾነ የቅዱሳት መጻሕፍት ሥነ አፈታት መርሆዎች በመጠቀም የሚያትቱ ሰባክያን፥ አስተማሪዎችና መሪዎችን ማዘጋጀት፤
🛐 በሥነ አመራር አስፈላጊ ሥልጠና አግኝተው ክኅሎታቸውን ያደበሩ ሥልጡን አገልጋይ መሪዎች ለክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ማዘጋጀት፤ በቃለ እግዚአብሔር ሥር በመኖር፥ ጤናማ የነገረ መለኮት ዕውቀትን በተግባር በመግለጽና በኢትዮጵያ ዐውድ በማዛመድ በሕይወታቸውና በአገልግሎታቸው ለሌሎች ምሳሌ የሚኾኑ አገልጋዮችን ማፍራት፤ እና
🛐ለስብከተ ወንጌል ልዑክነት የማያመነቱና በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተሞልተው የጌታ ስም በማይታወቅበት ቦታና ማኅበረ ሰብ መካከል አብያተ ክርስቲያናትን በመትከል በተሰማሩበት ቦታዎች ኹሉ ፍሬያማ የሚኾኑ የወንጌል ልዑካንን ማዘጋጀት።
ዕሴቶቻችን
🛐የቅዱሳት መጻሕፍት የበላይነት
በኹሉም የነገረ መለኮት ኮሌጅ (የክርስቶስ ክብር ተስፍ የኮሌጅ)መርሐ ግብሮችና የዕለት ተለት እንቅስቃሴዎች ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ማዕከላዊ ነው።
🛐የኢትዮጵያውን ክብር ተሰፋ የነገረ መለኮት ማሰልጠኛ በማንኛውም የሕይወት አቅጣጫዎች መጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣናዊ ምንጭ መኾኑን ዕውቅና ይሰጣል።
🛐እኛ የኢትዮጵያውን ክብር ተሰፋ የነገረ መለኮት ማሰልጠኛ ያለን ኹላችን ሐሳባችንና ተግባራችን በሙሉ ለቃለ እግዚአብሔር ለማስገዛት እንፈልጋለን።
በግለ ሰቦች ሕይወት ውስጥ፥ በቤተ ክርስቲያንና በኅብረተ ሰብ መካከል ቅዱሳት መጻሕፍት ለውጥ የማምጣት ኀይል እንዳላቸው እናረጋግጣለን።
🛐የስብከተ ወንጌል ተልዕኮ
ሰዎች የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ አምላክነት እንዲያውቁ እንዲሁም፥ ግለ ሰባዊ ድኅነት፥ ማኅበረ ሰባዊ ለውጥና ባህላዊ ተሐድሶ በማምጣት ረገድ እግዚአብሔር በመላለሙ ላይ ያለውን የመንግሥቱን አገዛዝ እንዲገነዘቡ ለመርዳት ያስችለን ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ታላቅነትና የአደራረግ መንገዱ ለመገንዘብ እንናፍቃለን።
#ጸሎት
🛐ሕያው አምላክ እግዚአብሔር እንደ ፈቃዱ ምክር የአማኞችን ጸሎት የሚሰማና የሚመልስ መኾኑን አጥብቀን እናምናለን።
🛐ከእርሱ ጋር የጠበቀ ኅብረታችንን ለማጽናትና በክብር ተስፋ ኮሌጅ የሚከናወኑትን ነገሮች ኹሉ ለእግዚአብሔር ክብርና ለቤተ ክርስቲያን መታነጽ እንዲጠቀምበት ጸሎትን ከዐበይት ክርስቲያናዊና የአገልግሎት ተሞክሮዎቻችን ልንነጥል እንደማይገባ እናረጋግጣለን።
#መንፈሳዊ መነቃቃት
🛐ክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት በማንኛውም መንገድና ኹኔታ ከእግዚአብሔር ጋር በሚደረግ ወትሯዊ ኅብረት መድመቅ እንዳለበት እንገነዘባለን፤ ይህ ኅብረት በቃለ እግዚአብሔርና በመንፈስ ቅዱስ የጸጋ ኀይል የሚቀጣጠል መኾኑን በማመን የቅዱሳት መጻሕፍትና የነገረ መለኮት ጥናት ከግላዊም ኾነ ከኅብረት መንፈሳዊ መነቃቃትና የጸጋ ስጦታዎች አደራረግ እንዳይነጠል እንተጋለን።
#ሎሌያዊ አገልግሎት
እኛ የኢትዮጵያውን ክብር ተሰፋ የነገረ መለኮት ማሰልጠኛ ማዕከል የምንገኝ ኹሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከተቀበልነውና በባለ አደራነት ከተሰጠን ውጭ የምንመካበት እንዳይኖረን እንሻለን።
🛐 ክብር የሚገባው አምላክ እርሱ አባታችን ነውና ለአገልግሎት እንዳሰማራን እንገነዘባለን። ስለኾነም፥ እግዚአብሔርን ለማክበርና ሕዝቡን ለማገልገል የጠራን አምላክ በሚሰጠን ጸጋ የአልጋይነት አቋምና የሕይወት ጠባይ ይዘን ለመመላለስ እንሻለን።
#ብዝኀነት
🛐ከልዩ ልዩ ትውፊታዊ ዳራዎችና አብያተ ክርስቲያናት ከሚመጡ ወገኖች ለመማር መቻልን ዋጋ እንሰጣለን። ለተለያዩ አመለካከቶች ክፍት በመኾንና በእውነት ቃል በመመዘን የምንመላለስ ቢኾንም፥ ከሌሎች ልንማር በምንችለው ላይ ከማተኰር ይልቅ በልዩነታቸው ምክንያት እንዳንገፋቸው እንጠነቀቃለን።
አካዳሚያዊ ልዕቀት
አስተውሎት በተሞላው አዕምሯዊ ብስለት እግዚአብ ሔርን የማምለክን አስፈላጊነት፥ ጥብቅ በኾነ መንገድ ለምናካኺደው የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት እና በሳል ሒሳዊ ትንታኔ ለምናከናውንበት ዐውድ የማያወላውል ዐቋም ያለው ዋጋ እንሰጣለን።
ወስብሀት ለእግዚአብሔር